Positive Action for Development (PAD) በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በመሆን ለሁለተኛ ግዜ በድሬዳዋ ከተማ ጎዳናዎች ላይ ኑሯቸውን በመግፋት ላይ የሚገኙ ከ199 በላይ ታዳጊዎችን ለመኖሪያነት ወደ ተዘጋጀ ማዕከል እንዲገቡ ተደርጓል። Positive Action for Development (PAD) ከድሬዳዋ ከተማ እነዚህን ጨምሮ በአጠቃላይ 309 ታዳጊዎችን ከጎዳና ላይ የማንሳት ስራ እንደተሰራና የተለያዩ አገልግሎቶችን እየሰጠን እንገኛለን።
በዚህ አጋጣሚ የሴቭ ድሬ የበጎ ፍቃደኞች ህብረት እና የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ወደ ማዕከሉ ለገቡ ልጆች የተለያዩ የጤና አገልግሎቶችን ናተግባራት ከለሊቱ 11:30 ጀምሮ በማቆያ ማዕከሉ በመገኘት ስላደረገት ድጋፍ ከለብ እናመሰናለን።